ጆርድ ፍሎይድ፡ የጥቁር አሜሪካዊው ግድያ ተከትሎ በሚኒያፖሊስ ተቃዋሚዎች እና ፖሊስ ተጋጩ

您所在的位置:网站首页 52818879 ጆርድ ፍሎይድ፡ የጥቁር አሜሪካዊው ግድያ ተከትሎ በሚኒያፖሊስ ተቃዋሚዎች እና ፖሊስ ተጋጩ

ጆርድ ፍሎይድ፡ የጥቁር አሜሪካዊው ግድያ ተከትሎ በሚኒያፖሊስ ተቃዋሚዎች እና ፖሊስ ተጋጩ

2024-06-23 03:53| 来源: 网络整理| 查看: 265

ጆርድ ፍሎይድ፡ የጥቁር አሜሪካዊው ግድያ ተከትሎ በሚኒያፖሊስ ተቃዋሚዎች እና ፖሊስ ተጋጩ27 ግንቦት 2020ፖሊስ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ለመተኮስ ተገዷል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ፖሊስ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ለመተኮስ ተገዷል

በሚኒያፖሊስ ከተማ ነጭ ፖሊስ ያልጣጠቀ ጥቁር አሜሪካዊ አንገትን በጉልበቱ እረግጦ ለሞት ማብቃቱን ተከትሎ በአሜሪካ ቁጣ ተቀስቅሷል።

በሜኒሶታ ግዛት ሚኒያፖሊስ ከተማ ፖሊስ እና ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ተጋጭተዋል። በብስጭት አደባባይ የወጡት ሰልፈኞች ፖሊስ ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ ፖሊስ ሰልፈኞቹን ለመበተን አስልቃሽ ጭስ ተኩሷል።

በማኅበራዊ ሚዲያ በአስደንጋጭ ፍጥነት በተሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይ ነጭ ፖሊስ እጁ ወደኋላ የታሰረውን ጥቁር አሜሪካዊ አንገት በጉልበቱ ተጭኖት ፊቱን ከመሬት አጣብቆ ይዞት ይታያል።

በሚኒሶታ በነጭ ፖሊስ ታንቆ የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ጉዳይ ቁጣን ቀሰቀሰ

ጥቁር አሜሪካዊው በበኩሉ "መተንፈስ አልቻልኩም እባክህን አትግደለኝ" እያለ ሲማጸነው ይሰማል። ይህ ነጭ ፖሊስን ይህን ሲፈጽም ሌሎች ሦስት ፖሊሶች ከጎኑ ቆመው ነበር።

ሟቹ የ46 ዓመት ጎልማሳ ጆርጅ ፍሎይድ ይባላል።

አራቱ ፖሊሶች ከሥራ መባረራቸው ተነግሯል።

ይህ ዘግናኝ ክስተት ከዓመታት በፊት በተመሳሳይ ቁጣን የቀሰቀሰውና በነጭ የፖሊስ አባላት ጭካኔ የሞተውን ኤሪክ ጋርነርን ያስታወሰ ሆኗል። ኤሪክ በወቅቱ በፖሊስ አንገቱ ተቆልፎ "እባካችሁ መተንፈስ አልቻኩም" እየለ ነበር የሞተው።

በተቋሞ ሰልፉ ምን ተፈጠረ?

የታቀውሞ ሰልፎቹ የጀመሩ በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ማክሰኞ ከሰዓት ነው። ሰዎች ነጩ ፖሊስ ጥቁር አሜሪካዊውን አንቆ የያዘበት ስፍራ ለተቃውሞ ተሰባስበዋል።

የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጆቹ ሰዎች ርቀታቸውን እንዲጠበቁ እና የታቀውሞ ሰልፉ ሰላማዊ እንዲሆን ሲጥሩ ነበር። ለሰልፍኞቹ "መተንፈስ አልቻለኩም" እና "እኔ ልሆን እችል ነበር" የሚሉ መፈክሮችን ደጋግመው ሲያሰሙ ነበር።

ለተቃውሞ አደባባይ የወጣች ሴት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

አንድ ለተቃውሞ ሰልፍ የወጣች ሴት ለሲቢኤስ "ይህ እጅግ አስቀያሚ ነገር ነው። ፖሊስን ይህን አይነት ሁኔታ የፈጠረው እራሱ መሆኑን ማወቅ አለበት" ብላለች። ሌለኛው ሰልፈኛ ደግሞ "ተንበርክኬ የሰላም ምልክት እያሳኋቸው አስልቃሽ ጭስ ተኮሱብኝ" ብሏል።

ፖሊስ ለተቃውሞ ከወጡት መካከል አንዱ በጥይት መመታቱን ያስታወቀ ሲሆን፤ ግለሰቡ የደረሰበት ጉዳት ህይወቱን አደጋ ላይ የሚጥል አይደለም ከማለት ውጪ ዝርዝር መረጃ ሳይሰጥ ቀርቷል።

የሆነው ምን ነበር?ፖሊስ

የፎቶው ባለመብት, Darnella Frazier

ሰኞ በሚኒሶታ ሜኒያፖሊስ ያጋጠመው ክስተት ለ10 ደቂቃ ያህል የቀረጹ የአይን እማኞች ፖሊሱ ጉልበቱን ከተጠርጣሪው አንገት እንዲያነሳ ሲጠይቁት በተንቀሳቃሽ ምሥሉ ይታያል።

በምሥሉ ላይ ሟችም "መተንፈስ አልቻልኩም ከማለቱም በላይ እባክህን አትግደለኝ" እያለ በተደጋጋሚ ሲማጸን ያሳያል።

ሌላ የዐይን እማኝ "እባክህን አፍንጫውን እየነሰረው ነው" ሲል ፖሊሱን ይማጸነዋል። ፖሊሱ ምንም ምላሽ አይሰጥም፤ ሆኖም ሌላ የፖሊስ ባልደረባ ቀረጻውን በመከለል ለማስተጓጎል ሲሞክር ይታያል።

የ Facebook ይዘትን ይለፉት, 1

የሚፈልጉት ይዘት የለም

በ Facebook ተጨማሪ ይመልከቱቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም.

የ Facebook ይዘት መጨረሻ, 1

በቪዲዮው ላይ ሌላ የዐይን እማኝ "አሁን የገደልከው ይመስለኛል፤ ይህ ድርጊትህ ሕይወትህን ሙሉ ይከተልሃል" ሲል ይሰማል።

ከዚህ በኋላ ተጠርጣሪው እንቅስቃሴ አልባ ሆኖ ይዝለፈለፋል። አምቡላንስ መጥቶም ይወስደዋል። ምናልባት ግለሰቡ በዚያው ቅጽበት ሞቱ እንደሆነም ተጠርጥሯል።

ፖሊስ ግን ግለሰቡ የሞተው ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ነው ይላል።

ጆርድ ፍሎይድ

የፎቶው ባለመብት, Twitter/Ruth Richardson

የምስሉ መግለጫ, ጆርድ ፍሎይድ


【本文地址】


今日新闻


推荐新闻


CopyRight 2018-2019 办公设备维修网 版权所有 豫ICP备15022753号-3